ሜካትሮኒክስ ቴክኒሻን
ስራህን አሳየኝ! ሜካትሮኒክስ ቴክኒሻን
ማንቃት ያስፈልጋል
ይህን ቪዲዮ በመጫን የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ማየት ይችላሉ፤ከነቃ በኋላ ዳታ ወደ ዩቲዩብ እንደሚተላለፍ ልንገልጽልዎ እንወዳለን። በገጹ ላይ በማንኛውም ጊዜ ይህንን ማንቂያ ማጥፋት ይችላሉ፡፡ ግላዊነት.
የሜካትሮኒክስ ቴክኒሻን ስራ ምንድነው?
የሜካቶኒክስ ቴክኒሻኖች እንደ ሮቦቶች ከመካኒካል፣ ከኤሌክትሮኒካዊ እና ከኤሌትሪክ አካላት የተውጣጡ ውስብስብ የሜካትሮኒክ ስርዓቶችን ይገነባሉ። የተለያዩ ክፍሎችን ፈትሽው ያስተከክላሉ። የተጠናቀቁ ሲስተሞችን ስራ ላይ ያውላሉ እና ተያያዥ ሶፍትዌሮች በፕሮግራም ተዘጋጅተዋል ይጭናሉ። ይህ የሚከናወነው በእቃው ንድፎች እና የንድፍ ስዕሎች መሰረት ነው። አንድ ሲስተም ለደንበኛው ከመሰጠቱ በፊት መሞከር አለበት። የሜካቶኒክስ ቴክኒሻን አስፈላጊ እና ዋናው ተግባር ጥገና ነው። ይህ የሜካኒካል ስርዓቶችን በየጊዜው መመርመርን ያካትታል። በዚህ መንገድ የተበላሹ ነገሮች ጉዳት ሳያደርሱ ሊታረሙ ይችላሉ። ይህ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ እንዳይበላሽ ይከላከላል።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- ትጋት (ለምሳሌ ጉድለቶችን በመተንተን እና ማረም)
- ቴክኒካል ግንዛቤ ጥንቃቄ
- ብልሀት እና የአይን-እጅ ቅንጅት (ለምሳሌ ክፍሎች ሲሰበሰቡ እና ሲተኩ)
ለሜካትሮኒክስ ቴክኒሻን የሚሆኑ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።