የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ባለሙያ
ስራዎን ያሳዩ! የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ባለሙያ
ማንቃት ያስፈልጋል
ይህን ቪዲዮ በመጫን የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ማየት ይችላሉ፤ከነቃ በኋላ ዳታ ወደ ዩቲዩብ እንደሚተላለፍ ልንገልጽልዎ እንወዳለን። በገጹ ላይ በማንኛውም ጊዜ ይህንን ማንቂያ ማጥፋት ይችላሉ፡፡ ግላዊነት.
የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ባለሙያ ስራ ምንድነው ?
እንደ ኢንደስትሪ ኤሌትሪክ ባለሙያ የኤሌክትሪክ ስራዎችን ይሰራሉ። በሠራተኛ ደህንነት መሰረት በኩባንያው ውስጥ ለምሳሌ ለኤሌክትሪክ ስራዎች ኃላፊነት አለብዎት። ከመጀመሪያው ጀምሮ ከሁሉም መስኮች መካከል በመምረጥ እና በመረጡት መስክ መስራት ይችላሉ። ስራዎ መገጣጠም እና የሜካኒካል ክፍሎችን ማገናኘት ፤ የኤሌክትሪክ ስርዓቶችን መመርመር እና በትክክል መስራታቸውን ማረጋረጥ፤ በሌላ አነጋገር በኤሌክትሪክ ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎችን ይከላለላሉ።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- እንክብካቤ (ለምሳሌ የኤሌክትሪክ እና ሜካኒካል ተግባራትን ሲፈትሹ እና ሲለኩ)
- ጥንቃቄ (ለምሳሌ ቀጥታ ክፍሎች እና የቮልቴጅ ግንኙነቶች ላይ ሲሰሩ)
- ቴክኒካዊ ግንዛቤ (ለምሳሌ መሣሪያዎችን እና ስርዓቶችን ሲንከባከቡ)
- ቅልጥፍና (ለምሳሌ ገመዶችን ሲሰበስቡ እና ሲፈቱ)
ለኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ሰሪዎች ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።