ንድፍ
ይህ የሙያ ዘርፍ በፈጠራ ላይ ያተኩራል። የሚሰሩት ስራዎች በዲጂታል ሚዲያ በመጠቀም ወይም በእጅ በሚሰሩ ስራዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- ትዕግስት ፤ የማተኮር ችሎታ እና ትክክለኛነት
- ቅልጥፍና እና የዓይን-እጅ ቅንጅት
- የቀለም እና ቅርጾች ፈጠራ ብቃት
- የደንበኛ መንከባከብ ዝንባሌ (ለምሳሌ ደንበኞችን ሲመክር፣ በሽያጭ ላይ)
በንድፍ ዘርፍ ያሉ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።