ንግድ እና አስተዳደር
በቢሮ ውስጥ ባሉ የሂደቶች አደረጃጀት ፤ መርሐግብር እና ትዕዛዝ ላይ ያተኩራል። የተለመዱ የስራ ቦታዎች፣ ለምሳሌ አስተዳደር፣ ግብይት እና ማስታወቂያ፣ ኢንሹራንስ፣ የሰው ሃይል ወይም የሪል እስቴት አስተዳደር ናቸው። በሽያጭ እና በስርጭት ውስጥ ትኩረቱ በሁሉም ዓይነት እቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ ነው። በሂሳብ አያያዝ ወይም በግብር ጉዳዮች ላይ እንደሚደረገው የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማቀድ እና ለማቀናጀት የንግድ ሥራ አመራር እና የህግ መርሆዎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- የደንበኛ እና የአገልግሎት አይነት ማወቅ
- ማገናዘብ መቻል
- ድርጅታዊ ችሎታዎች
- የኮምፒውተር እውቀት
ይህ የስራ ዘርፍ የሚስማማዎ ከሆን የ ንግድ እና አስተዳደር KoJACK መልምውጃዎችን ይውሰዱ !
በንግድ እና አስተዳደር ዘርፍ ያሉ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።