የቢሮ ረዳት
የቢሮ ረዳት ስራ ምንድነው?
የቢሮ ረዳቶች ሁሉን አቀፍ ናቸው እና ነገሮች በቢሮ ውስጥ ያለችግር መሰራታቸውን ያረጋግጣሉ። በማንኛውም ቦታ መሰማራት እና እርዳታ በሚያስፈልግበት ቦታ ሁሉ ድጋፍ መስጠት ይችላሉ። ደብዳቤዎችን ይቀበላሉ እንዲሁም ማህተም ያደርጋሉ። ስራዎችን ያከነውናሉ ፤ ሰነዶችን ያስተካክላሉ፤ በተጠቀሰው ቅደም ተከተል አንድ ላይ ያስቀምጧቸዋል እና የመሰብሰቢያ ክፍሎችን ያዘጋጃሉ። በስልክ ላይ ተግባቢ መሆን ይጠበቅቦታል እና ምን መረጃ ጠቃሚ እንደሆነ መገምገም አለቦት። የክፍያ መጠየቂያ ሰነዶችን ማጠናቀር እና ማዘጋጀትም የስራው አንድ አካል ነው።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- ድርጅታዊ ክህሎቶች እና ትጋት
- ጥሩ የቃል እና የጽሁፍ መግለጫ
- የኮምፒውተር እውቀት
ለቢሮ ረዳት የሚሆኑ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።