አስጎብኝ
ይህ ሙያ ከቱሪስቶች ጋር አብሮ መስራት እንዲሁም በከተማ ወይም በገጠር ውስጥ ታዋቂ ቦታዎችን ማስጎብኘትን ያካትታል።
የአስጎብኝ ስራ ምንድነው?
እንደ አስጎብኚ፣ አስደሳች እና የተለያየ የዕለት ተዕለት ተሞክሮ ሊኖሮት ይችላል። አስጎብኝ ለጎብኝዎች መመሪያዎች፤ታሪክን፣ ተግባራቶች፣ ልማዶች፣ የአንድ የተወሰነ ክልል ተፈጥሮ እና ሀገራትን መረጃዎ ይሰጣሉ። የአስጎብኚው ኃላፊነቶች የጉዞ መርሐግብሮችን ማቀድ፣ ደንበኞችን ከአካባቢው ጋር በተሽከርካሪ ወይም በእግር ማስተዋወቅ እና ቡድኑ በማንኛውም ጊዜ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥን ያጠቃልላል። እንዲሁም ደንበኞችን ሊስቡ በሚችሉ አዳዲስ መስህቦችን ማወቅ ሲሆን ይህንን ለማድረግ የተሻላ መረጃ ሊኖራቸው ይገባል። እንደ አስጎብኚነት ስኬትን ለማረጋገጥ፣ ለደንበኞች አገልግሎት ጥሩ ችሎታ ያለው ጥሩ ታሪክ አዋቂ መሆን አለቦት። ደንበኞችዎ የውጭ ዜጎችን ስለሚያካትቱ፣ የተለያዩ ባህሎችን እና ቋንቋዎችን ማወቅ ይኖርቦታል። አንድ ጥሩ የሚባል አስጎብኚ ለእያንዳንዱ የጎብኝዎች ቡድን ልዩ ፍላጎት የሚስማማ ነገር ማድረግ ይኖርባታል።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- የተግባቦት ችሎታዎች
- የጭንቀት መቋቋም ችሎታ
- የደንበኛ የአገልግሎት አሰጣጥ እውቀት
- ከነገሮች ጋር የመላመድ ችሎታ
በአስጎብኝነት ዘርፍ ያሉ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።