የጽዳት ሰራተኛ
የጽዳት ሰራተኛ ስራ ምንድነው ?
የተለያዩ ህንጻዎች እና የግል ቤተሰቦችን ውስጥ እና ውጪ ያጸዳሉ። ለምሳሌ የሕዝብ ሕንፃዎችን እንደ ሆስፒታሎች፣ ቢሮዎች፣ ጂምናዚየሞችን እና የመዋኛ ገንዳዎችን ያጸዳሉ። በግል ቤት ውስጥ ሁሉንም ዓይነት የጽዳት ስራዎችን ያከናውናሉ። ለአንድ ጊዜ ሥራ ወይም ለሳምንታዊ ስራ ሊቀጠሩ ይችላሉ። ሁሉም በደንበኛው ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው.
ይህ የሙያ ዘርፍ በንፅህና እና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ብዙ እድሎችን ይሰጣል። ለምሳሌ በአካባቢ ላይ ብዙም ተጽእኖ ስሌላቸው አማራጭ የጽዳት ዘዴዎች ይማራሉ።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- ጥሩ የአካል ሁኔታ (ለምሳሌ ለረጅም የጉልበት ስራዎችን ለመሥራት)
- እንክብካቤ እና የኃላፊነት ስሜት
- ታማኝነት/አስተማማኝነት (ሰዎች ቤት ውስጥ ስለሚሰሩ)
- የማጽዳት ፍላጎት
ለጽዳት ሰራተኛ የሚሆኑ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።