የአትክልት እና ፍራፍሬ አትክልተኛ
ይህ የሙያ ዘርፍ ተክሎች ስለማደግ እና መንከባከብ ነው።
ስራዎን ያሳዩ ! አትክልተኛ
ማንቃት ያስፈልጋል
ይህን ቪዲዮ በመጫን የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ማየት ይችላሉ፤ከነቃ በኋላ ዳታ ወደ ዩቲዩብ እንደሚተላለፍ ልንገልጽልዎ እንወዳለን። በገጹ ላይ በማንኛውም ጊዜ ይህንን ማንቂያ ማጥፋት ይችላሉ፡፡ ግላዊነት.
የአትክልተኛ ስራ ምንድነው?
አትክልተኛ ከተፈጥሮ ጋር በቅርበት የሚሰራ ሲሆን በተክሎች እንክብካቤ እና ምርታማነት ላይ ያተኩራል። አፈር መንከባከብ ፤ መደብ መስራት ፤ ተክሎችን ማብቀል ፤ውሃ ማጠጣጥ እና ማዳበሪያ መጨመርን ያካትታል እንዲሁም የምርት ስብሰባን ያካትታል። በተጨማሪ ደንበኞችን ማማከር ፤ ምርት መሰብሰብ ፤ ሽያጭ (ጅምላ ወይም ችርቻሮ) ን ያጠቃልላል።
ለዚህ ስራ የሚያስፈለገው ምንድነው ?
- የእጅ ጥበብ (ምሳሌ የተለያዩ መሳሪያዎችን መጠቀም)
- አስቀድሞ ማሰብ እና እንክብካቤ (ምሳሌ እጽዋት ጥበቃ እና ማዳበሪያ አጠቃቀም ላይ )
- ጥንካሬ እና አካላዊ ችሎታ
- የተፈጥሮ እና የአካባቢ እውቀት
ለአትክልተኛ የሚሆኑ ኮርሶች
ደረጃ 1=መሰረታዊ ደረጃ ለሙያው የመጀመሪያ የሆኑትን መሰረታዊ ነገሮች ለመስጠት የሚረዳ ነው፣ለሙያወ አቅጣጫ ለማስያዝ ይረጋል። ደረጃ 2 = መካከለኛ ደረጃ መሰረታዊ ትምህርት ለተማሩ እና ስለሙያ የበለጠ ዝርዝር እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ነው። ደረጃ 3 = የላቀ ደረጃ ማለት በአንድ የተወሰነ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድሞውኑ እውቀት ላላቸው እና በዚያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስለ ዝርዝር ነገሮች እውቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ደረጃ 4=ፕሮፌሽናል ደረጃ የተነደፈው ስራ እየሰሩ ላሉ እና ለሙያው አዲስ እውቀት እና ክህሎት ማግኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ነው።