የመማሪያ ቅርጸቶች
ታዲያ ይህን ሁሉ እንዴት ይማራል? ትምህርት እንዴት ይከናወናል?
መማር ድንገተኛ ነው ፤ የመጀመሪያው ደረጃ ጤነኛ ሰው በርግጥ በመጀመሪያ መማር ላይጠበቅበት ይችላል፤ ሆኖም የማናውቀው ሀይል እራሳችንን እንድንገልጥ ይረዳናል።ትንንሽ ልጆችን ከተመለከቱ ፤ ይህን በቀላሉ መረዳት ይችላሉ።
ያለማቋረጥ እና በደስታ ይማራሉ!
ልጆች በራሳቸው፣ በነፃነት፣ በደስታ፣ በብርቱነት፣ በሙሉ ስሜታቸው እና ያለ ሽልማት ይማራሉ።
ቢሆንም፣ በወጣቶችና በጎልማሶች ዘንድ ይህ የመማር ጉጉት በጣም እየቀነሰ አልፎ ተርፎ እየቀነሰ ሲሄድ ይታያል።
እዚህ ላይ ጥያቄው ይነሳል፤ "የሚፈጠረው ምንድነው የመጀመሪያ የሕይወት ኃይላችን ይከስማል፤ ስለዚህ ይህ ኃይል እንደገና እንዲያብብ ምን መሰናክሎች እና እገዳዎች መወገድ አለባቸው ?
ወሳኙ እና ፍሬያማ ጥያቄው፡- "በትክክል ሰዎች እንዳይማሩ የሚከለክለው ምንድነው?"
አዳዲስ የማስተማር እና የመማር ዓይነቶች በየጊዜው እየታዩ ነው ነገር ግን በጣም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የመማር ሂደቶች ተደራጅተው ይገኛሉ ። የመማር ፎርማት እንደ የተለየ ሜተዶጅካል-ዳዳክቲክ አቀራረብ ይታያል እናም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ይተገበራል።
ከተለምዶዊ የማስተማር ዓይነቶች በተቃራኒ እነዚህ ከመማር ወደ ትምህርት፣ ከመመሪያ ወደ ተሳትፎ፣ ዕውቀትን ከማስተላለፍ ወደ ስልታዊ ልዩነት ወዳለው የመማሪያ አካባቢ በመቀየር ይታወቃሉ። በተለይም በአዲስ ሚዲያ (ኢ-ትምህርት፣ የተቀናጀ ትምህርት) መማርን ያካትታል።
አንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች እዚህ ቀርበዋል፡-
የክፍል ውስጥ ትምህርት፡ የክፍል ውስጥ ትምህርት ተለምዶዊ የማስተማር ሂደት ሲሆን የመማሪያ ሂደቱ በክፍል ውስጥ ነው። በክፍል ውስጥ ተማሪውም አስተማሪውም መገኘት አለባቸው።
የመመሪያ ትምህርት ራስን በራስ ማስተማር : በአስተማሪዎች የሚታገዝ የትምህርት አይነት። መመሪያ አንዱ የማስተማር መንገድ ነው። ይህም የመማሪያ ቦታ ማመቻቸት ያክትታል. ራስን በራስ ማስተማር ይህ የማስተማር አይነት ግለስቦች ሙሉ የመማር ሂደት (ማቀድ ፤ መማር ፤ ማጥናትና የመሳሰሉትን) የሚያሃሂዱበት ነው ።
ሴሚናሮች: ሀሳቦችን የሚነሱበትና እና የሚጎለብትበት ቦት ነው። ከንግግሮች በተለየ የሴሚናር ክፍሎች ለየት ያለ እንዲሆኑ የታቀዱ ተማሪዎች ፕሮፌሰሮችን ብቻ ከማዳመጥ እና ማስታወሻ ከመያዝ ይልቅ በውይይት ውስጥ ይሳተፋሉ። ሴሚናሮች በንግድ እና ሙያዊ እድገት ውስጥ ባሉ ልዩ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቀጥታ ፣ አነስተኛ ቡድን ውይይቶችን ይፈቅዳሉ።
የተቀናጅ ትምህርት: ኢ-ትምህርት፣ በተጣመረ ትምህርት የሁለቱም አለም ምርጡን የማስተማሮያ መንገድ፣ ዲጂታል እና አናሎግ ያጣምራል። የተቀናጀ ትምህርት በአዳዲስ ዲጂታል አማራጮች አጠቃቀም እና የመማር ዓላማዎች እና በተማሪዎቹ አስፈላጊ ብቃቶች መካከል ምርጡን ጥመርታ ይፈጥራል።
የስራ ቦታ ትምህርት: በሥራ ቦታ ውስጥ የመማር እና የመማር ሂደቶችን ይመለከታል። ለምሳሌ፣ በስራ ላይ መማር ወይም እየሰሩ መማር። የስራ ቦታ መማር ለግለሰቦች ትምህርት የሚሰጡ ልዩ አስተዋጾዎች በስራ እንቅስቃሴዎች እና በስራ ቦታዎች ወይም የስራ ልምዶች ውስጥ በመሳተፍ የሚቀርቡ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ያጎላል።