ተግባቦት
የአሰልጣኞች እንቅስቃሴ ብዙ ውይይት ማድረግን ያካትታል
በሁሉም የስትራቴጂካዊ ጠቃሚ የመማሪያ ነጥቦች ላይ ውይይት አለ፡-
ትምህርቱ ውይይት ያስፈልገዋል እንድ የመማር ስምምነት ውይይት፤ የርክክብ ውይይት ፤ጊዜያዊ ውይይት ፤ የመጨረሻ ውይይት - እና ይህ ዝርዝር ሊቀጥል ይችላል በተጨማሪም የዝግጅት አቀራረብ ውይይቶች፤ የግጭት ውይይቶች ፣ የምክር ውይይቶች ፣የግብ ስምምነት ውይይቶች፤ ወ.ዘ.ተ ያካትታል ። በአጭሩ
ዘመናዊ ትምህርት እና ስልጠና በመሠረቱ በውይይት መልክ የሚከናወነውን ነው።
ለአንዳንድ አሰልጣኞች ይህ የውይይት አጽንዖት ትልቅ ፈተና ነው።
በትምህርት ማስተባበር ተግባቦት ውስጥ አንድ ነገር መነገሩ ብቻ ሳይሆን ከሁሉ በላይ የሆነ ነገር እንዴት መነገር እንዳለበት ማወቁ ነው። ይህም በሰዎች መካከል ያሉ ግንኙነቶች እና ተግባቦቶችን ሊያመቻች ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊያግድ ይችላል። አሰልጣኞች እገዳዎችን ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ ፍላጎት ሊኖራቸው ይገባል።
በረጅም ጊዜ ውስጥ በተደረጉ የተግባቦት ምርምሮች ስለ ሰው ግንኙነት እና ግንኙነትን ስለሚያበረታቱ እና ስለሚያደናቅፉ ብዙ ግኝቶች ተገኝተዋል።
ተግባቦት መረጃን ማስተላለፍ ብቻ አይደለም በተጨማሪም ጥረትን ያበረታታል፣አመለካከትን ያሻሽላል እና አስተሳሰብን ያነቃቃል። ያለ እሱ ፣ የተዛቡ አመለካከቶች ይገነባሉ ፣ መልእክቶች ይበላሻሉ እና ትምህርት መስጠት አስቸጋሪ ይሆናል ። ተገባቦት መደማመጥ ጠቃሚ ሚና የሚጫወትበትን መረጃ የመረዳት እና የመለዋወጥ ሂደት ነው።
በተግባቦት ዘርፍ ያሉ ትምህርቶች
Basic course in human communication
This course will show how human communication works.