ቢና የሙያ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ
ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የሙያ ስልጠና እና ቅጥር
የባቫሪያ ወጣቶችን በማሰልጠን ረገድ ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጡ መዋቅሮች በአፍሪካ አህጉርም ጥቅም ላይ ይውላሉ። ይህ ትኩረቱ ስልጠና ብቻ አይደለም። አላማው በመጀመሪያ ላይ በሙያ ገላጻ ላይ በማተኮር የስራ ምደባንም ያካትታል።
የብቃት አሃድ
የመገለጫ ፤ የብቃት ግምገማ ፤ ተጨማሪ ትምህርት / የሰው ኃይል ልማት ፤ የሥራ ገበያ ፖሊሲ
ተሳተፊዎች
መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ሰልጣኞች፣ ስራ አጥ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ የሰለጠነ ሰራተኛ የሚፈልጉ ኩባንያዎች
የፕሮጀክት ቆይታ
07.2019 – 12.2021
ሀገር
ኢትዮጵያ
በንግዱ ዘርፍ የወደፊት ሰልጣኞች ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምን ምን ናቸው? አንድ ወጣት ምን ቅድመ ሁኔታዎች ሊኖረው ይገባል? ፕሮፋይሊንግ በሙያ አቀማመጥ አውድ ውስጥ አስፈላጊ መሳሪያ ነው። ይህንን እና ሌሎች የስልጠና መሳሪያዎችን እና ዘዴዎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ ፍላጎት ማበጀት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ የሙያ ትምህርት ቤት ለማቋቋም ቢና ፕሮጀክት አላማ ነው።
ከግሉ ሴክተር ጋር በመተባበር የተደረገ ተግባራዊ አቀራረብ
Berufliche Fortbildungszentren der Bayerischen Wirtschaft (የባቫሪያን አሰሪዎች ማኅበራት የሥልጠናና ልማት ማዕከል) (bfz) በአዲስ አበባ ከምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሰላም ኮሌጅ ጋር በጋራ ይሰራል። አሰራሩ በተግባር የተደገፈ ነው፤ የሙያ ስልጠና ከግሉ ሴክተር ጋር በቅርበት አያይዞ ይሰጣል ። ለምሳሌ ፕሮጀክቱ በአንድ በኩል የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት ለመቅረፍ እና በተቻለ መጠን ብዙ ወጣቶችን ለማሳተፍ ፤በሌላ በኩል የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ ነው።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ሁለተኛዋ ትልቅ ሀገር እና አነስተና ገቢ ካላት ሀገር አንዷ ናት። ማህበራዊ ሁኔታዎች በተለይም ለወጣቶች አስቸጋሪ ናቸው። ጥሩ የሥልጠና እድሎች የወደፊት ችግሮችንና እና የውስጥ ፍልሰት ይቀንሳሉ።
የተሞከሩ እና እየተሞከሩ ያሉ መዋቅሮችን ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ማላመድ
የቢኤንኤ ፕሮጀክት ርእሶች ከክህሎት ምዘና እና የስራ አቅጣጫ እስከ የስልጠናው ይዘት እና ለወጣቶች ከስልጠና በኋላ የሚደረጉ የክትትል ድጋፎችን ያካተቱ ናቸው። ከግሉ ሴክተር ጋር በቀጥታ በመተባበር በተቻለ መጠን ብዙዎቹ ሥራ ማግኘት ማስቻል። ቀደም ሲል በሌሎች አገሮች በተሳካ ሁኔታ የሚሰሩ መዋቅሮች ከተለየ የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ማጣጣም ናቸው።
ምስራክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሰላም ኮሌጅ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ትልልቅ የትምህርት ተቋማት መካከል ሁለቱ ናቸው። በባቫሪያን ግዛት ቻንስለር የሚደገፈው የሀገር ውስጥ ፕሮጀክት በተለያዩ ደረጃዎች ይሰራል። መምህራኑን ከሰለጠኑ በኋላ እንደ እውቀት ማሻገሪያ ሆነው ይሰራሉ። ከbfz የመጡ አሰልጣኞች ምድብ በማውጣት እና በስራ ምደባ ዘርፍ ይደግፏቸዋል እና የቴክኒክ እውቀትን ያስተላልፋሉ። በኮሌጁ የቴክኒክ መሣሪያዎችን ማሻሻልም የፕሮጀክቱ አካል ነው።